በጸጥታ ችግር ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ባልተጀመረባቸው የምርጫ ክልሎችን የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባን ለማከናወን የጸጥታ ችግሮች እንቅፋት በሆነባቸው አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባ ከሚያዝያ 29 – ግንቦት 13 ቀን 2013 ድረስ በልዩ ሁኔታ እንዲራዘም ወስኗል።

በዚህም መሰረት ፣ በምእራብ ወለጋ ዞን ከ ቤጊ እና ሰኞ ገበያ ምርጫ ክልል ውጪ ፣ በምስራቅ ወለጋ ዞን (ከአያና እና ገሊላ ምርጫ ክልል ውጪ) ፣በቄለም ወለጋ ዞን እና በሆሮ ጉድሩ ዞን (ከአሊቦ፣ ጊዳም እና ኮምቦልቻ ምርጫ ክልል ውጪ) ከሚገኙት 31 ምርጫ ክልሎች መካከል በ24ቱ ላይ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በከማሽ ዞን ከሚገኙት አምስት የምርጫ ክልሎች በአራቱ የመራጮች ምዝገባ (ከሴዳል ምርጫ ክልል ውጪ)የመራጮች ምዝገባ ከሚያዝያ 29 – ግንቦት 13 ቀን 2013 ድረስ በልዩ ሁኔታ እንዲከናወን ወስኗል።

ከዚህም በተጨማሪ የመራጮች ምዝገባ በጸጥታ ችግር የተነሳ ሳይከናወንበት የነበረው የአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔር ልዪ ዞን የሚገኙት ዳዋ ጨፌ፣ ጨፋ ሮቢት እና ባቲ ምርጫ ክልሎች በተመሳሳይ ሁኔታ የመራጮች ምዝገባ ከሚያዝያ 29 – ግንቦት 13 ቀን 2013 ድረስ ይከናወናል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *