በተለያዩ ባህላዊ ትእይንቶች ታጅቦ የሚከበረው የፊቼ ጨምበላላ በዓል ዘንድሮ ደብዘዝ ባለ መልኩ እየተከበረ ይገኛል።

የዘንድሮ የፊቼ ጨምበላላ በዓል ከ ወትሮው በተለየ ሁኔታ በበዓሉ በጋራ ከሚከናወኑ ትውፊቶች ወጣ ብሎ የኮቪድ 19 ፕሮቶኮልን በጠበቀ መንገድ እየተከበረ እንደሚገኝ የሲዳማ ክልል ባህልና ስፓርት ቢሮ ዋና ሃላፊ አቶ ጃጎ አገኘው ለ ኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

እንደወትሮ ለበዓሉ ድምቀት የሆኑት እንደ ቄጠላና የመሳሰሉ ባህላዊ ጨዋታዎችም በጉዱማሌ አደባባይ እንደማይኖር ተነግሯል።

ይህንንም ታላላቅ የሃገር ሽማግሌዎች እና አባቶች በመምከር እና በመነጋገር ወረርሽኙ ሊያስከትለው የሚችለውን ጉዳት በመረዳት ህዝባዊ በሆነ መንገድ ሳይሆን ቤተሰባዊ አብሮነትን በጠበቀ መንገድ ቢከበር የተሻለ መሆኑን በመረዳት እንደተደረገ አቶ ጃጎ ነግረውናል።

ይሁን እንጂ ይህ አከባበር በየተቋማቱ፣በየወረዳውና በየቀበሌው እንደሚከበር ነው ሃላፊው የነገሩን።

እያንዳንዱ የበዓሉ አክባሪም ክብረ በዓሉን በየቤቱ ያክብር ሲባል እያንዳንዱ ቤተሰብ ከወዳጅ ዘመዱ ጋር በጥንቃቄ በመሰባሰብ ቤተሰባዊ አብሮነትን በመፍጠር፣ቤቱ ደጃፍ ላይ እርጥብ እንጨት ወይንም “ሁሉቃ “በመትከል የዚህንም ምሳሌ በሆነው በአንድነት በመሻገር ማክበር በመተሳስብ ማክበር እንደሚገባ አስታውቀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በቅርስነት የመዘገበው ይህ በዓል ዛሬ መከበር የጀመረ ሲሆን ለተከታታይ ሁለት ሳምንታትም እየተከበረ እንደሚቀጥል ሰምተናል።

የውልሰው ገዝሙ
ሚያዝያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *