የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነገ ለሚከበረው የዒድ-አልፈጥር በዓል ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ የሆኑ መንገዶችን ይፋ አደረገ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነገ በአዲስ አበባ ስታድዮም የሚደረገው የ1 ሺህ 442ኛው የዒድ አል-ፈጥር (ረመዳን) በዓል የዒድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለጊዜው ለተሸከርካሪ ዝግ የሆኑ መንገዶችን ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሠረት ነገ ከማለዳው 11:30 ሰዓት ጀምሮ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች፦

• ከ22 ወደ መስቀል አደባባይ
• ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከመስቀል ፍላወር አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኮካ ኮላ በከፍተኛው ፍ/ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
• ከበርበሬ በረንዳ በቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከቀድሞ ፈረሰኛ ፖሊስ በጌጃ ሰፈር ወደ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ
• ከተ/ኃይማኖት በጥቁር አንበሳ ወደ ጎማ ቁጠባ እና
• ከአትላስ ወደ ኡራኤል ቤተክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ናቸው።

አሽከርካሪዎች ይህንኑ አውቀው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ተባባሪ እንዲሆኑ እና በተገለጹት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም እና ለማንኛውም ፖሊሳዊ አገልግሎት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመረጃ ስልክ ቁጥሮች 011-1-11-01-11 እና በ991 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ ጨምሮ ገልጿል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *