ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በበይነ መረብ ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡

ከተመሰረተ 15 አመታት ያስቆጠረው ያርድስቲክስ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በበይነ መረብ አማካኝነት በአራት የትምህርት ዘርፎች በማስተርስ መርሀ ግብር ትምህርት መስጠት መጀመሩን የኮሌጁ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አዲስ መኮንን ተናግረዋል፡፡

በበይነ- መረብ አማካኝነት ትምህርት የሚሰጥባቸው የትምህርት ዘርፎች መካከል ፕሮጀክት ማኔጅመንት እና ቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ይገኙበታል፡፡

ተማሪዎች ከምዝገባ ጀምሮ መርሀ ግብሩን አጠናቀው የማስተርስ ሰርተፍኬታቸውን እስከሚወስዱበት ያለው ሂደት በበይነ መረብ ብቻ የሚከናወን ይሆናል ተብሏል።

ትምህርቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ የመማሪያ መጽሐፍት እና ሌሌችም ዲጅታላይዝድ መደረጋቸውም ተነግሯል።

በተጨማሪም የበይነ መረብ ትምህርት አካል ጉዳተኞችንም ያማከለ እና ተጠቃሚ የሚያደርግ ስርዓት እንደተዘረጋለትም ተጠቅሷል።

ኮሌጁ በመደበኛነት በ14 ቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች፣ በ4 ማስተርስ ፕሮግራሞችን ከ70 ባላነሱ በጥናት እና ዋና ማዕከላት ተደራሽ መሆኑን አስታውቋል።

ኮሌጁ የማስተርስ ፕሮግራም ትምህርትን በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችለውን ፍቃድ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ፍቃድ ማግኘቱን ኃላፊው አስታወቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *