ስፔን በሁለት ቀናት የጎረፉባትን ስደተኞች ለማስወጣት ወታደሮቿን አሰማርታለች፡፡

ቁጥራቸው እጅግ በርካታ ስደተኞች ከሰሜን አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሮኮ ተነስተው ወደ ሲውታ እንደደረሱ ያስታወቀችው ስፔን፤ እነዚህን ስደተኞች ወደ ግዛቷ አንዳይገቡ ለማድረግ በድንበሯ አቅራቢያ ወታደሮቿን አሰማርታለች፡፡

በስፔን ድንበር በሁለት ቀናት ውስጥ ወደ 8000 ሰዎች ወደ ሲውታ መድረሳቸውን የስፔን ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

አብዛኛዎቹ ስደተኞችም ይህንን ክልከላ ለማለፍ ሲሉ እየዋኙ ለመሻገር ሙከራ ማድረጋቸውም ተነግሯል፡፡

የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ይሄንን ሁኔታ አስተካክለዋለው ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡

በዚህም እርምጃ በባህር ዳርቻው የነበሩ አብዛኛው ስደተኞች ከስፍራው ላይ እንዲነሱ ወይንም እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡

ሳንቼዝ ቀውሱን ለመቋቋም እነዚህን ስደተኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ማድረጋቸው ሃገሪቱ ከሞሮኮ ጋር ያላት የዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ችግር ውስጥ እንዲገባ ማድረጉ ተነግሯል፡፡

ቢቢሲ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
የውልሰው ገዝሙ
ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *