አሜሪካ አሁንም ቢሆን የአካባቢውን ሰላም አደጋ ላይ ለመጣል አኮብኩባለች ስትል ቻይናን ከሰሰች

ቻይና የአሜሪካ የጦር መርከብ የታይዋንን የባህር ሰርጥ አቋርጦ ማለፉ አሜሪካ አሁንም ቢሆን ሰላምን አደጋ ላይ ለመጣል አኮብኩባለች ስትል ቻይና ከሳለች፡፡

የአሜሪካ የጦር መርከበኛ ከርቲስ ዊልበር እንደረጋገጡት ሃገሪቱ የጦር መርከቧን በርግጥም በታይዋን ባህር ላይ መጓዙን አምነው ነገር ግን ቻይና እንደምትለው አሜሪካ የቀጠናውን ሰላምና መረጋጋት አደጋ ላይ ለመጣል እንዳልሆነ በመግለፅ የቻይናን ውንጀላ አጣጥላላች፡፡

የአሜሪካ የባህር ኃይል እንዳሉት በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት መደበኛ በሆነ መልኩ በታይዋን የባሕር ሰርጥ ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት አካሂደናል፤ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይል አሁንም ቢሆን ዓለም አቀፍ ሕግ በሚፈቅደው ቦታ ሁሉ መብረሩን ሆነ መጓዙን ይቀጥላል ብለዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በሁለቱ ኃይሎች መካከል ከፍተኛ ውጥረት በተፈጠረበት በዚህ ወቅት የቻይና የምሥራቅ ዕዝ ቃል አቀባይ የአሜሪካ እርምጃዎች የተሳሳቱ እና ሆን ተብሎ የአካባቢውን ሰላም ለማወክ እና ነገር ፍለጋ ነው ስትል፤ የፈለገ ቢሆን ታይዋን ግዛቴ ናትና ያሻኝን ማዘዝ እችላለው የምትላት ታይዋን ግን አሁንም ቢሆን ከቻይና ገለልተኛ የሆነች ግዛት እንደሆነች በመግለፅ ላይ ናት፡፡

የታይዋኑ ፕሬዝዳንት ታሲኢንግ-ዌን እኛ ገለልተኛ ሀገር ነን ሲሉ በድጋሚ ተናግረዋል ፡፡

አልጀዚራ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
የውልሰው ገዝሙ
ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *