ለታላቁ የህዳሴ ግድብ እስካሁን 15 ቢሊዮን ብር ከህዝብ ተሰብሰቧል ተባለ፡፡

ኢትዮጵያዊያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ባደረጉት ተሳትፎ 15 ቢሊዮን ብር ማውጣታቸው ታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ሲሆን በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከህብረተሰቡ 15 ቢሊዮን ብር እንደተሰበሰበ ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ከባለድርሻ አካላት ጋር ስለ ግድቡ ግንባታ ሂደት ውይይት መካሄዱን አስታውሰዋል ።

የግድቡ አጠቃላይ የግንባታ ሂደት 80 በመቶ እንደደረሰና የዜጎች ተሳትፎውም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል ።

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ ማለትም በመጪው ክረምት እንደምታካሂድም አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።

ሁለተኛውን ዙር የግድቡን የውሃ ሙሌት በተመለከተ ግብፅ ጉዳት አያደርስብኝም ማለቷ የሚታወስ ነው።

የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹኩሪ የአስዋን ግድብ በቂ የውሃ ክምችት በመያዙ ኢትዮጵያ ግድቧን ብትሞላ ጉዳት አያደርስብንም ሲሉ ለሁለተኛ ጊዜ አረጋግጠዋል ።

ግብፅና ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ አቋማቸውን ሲለዋውጡ እንደነበር አይዘነጋም።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *