ሪቨር ፕሌት አማካዩን በግብ ጠባቂ ቦታ አሰልፎ አሸነፈ

ሪቨር ፕሌት በኮቪድ ምክንያት ተጫዋቾቹን በማጣቱ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹን ኤንዞ ፔሬዝ በግብ ጠባቂ ሚና እንዲያሰልፍ አስገድዶት ነበር፡፡

እንደዚያም ሆኖ በኮፓ ሊበርታዶሬስ (በደቡብ አሜሪካ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ አቻ ውድድር ) ኢንዲፔንዲዬንቴ ሳንታ ፌን 2ለ1 አሸንፏል፡፡

የአርጀንቲናው ክለብ 20 ተጫዋቾች በኮቪድ 19 ፖዘቲቭ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

ጉዳት የገጠማቸው ተጫዋቾች መኖራቸው ሲታከልበት በቡዌኖስ አይረስ በተደረገው የምድብ አራት ጨዋታ ለአገልግሎት ብቁ ሆኖ ያገኛቸው አጠቃላይ ተጫዋቾች ብዛት 11 ብቻ ነበር፡፡

የ35 ዓመቱ ፔሬዝ የቡድኑን ግብ እንዲጠብቅ ተመርጦ ቡድኑ አሸናፊ እንዲሆን አግዟል፡፡

ፋብሪዚዮ አንጊሌሪ እና ሁሊያን አልቫሬዝ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ሪቨር ፕሌት የኮሎምቢያውን ቡድን 2ለ0 እንዲመራ አስችለውታል፡፡

በ2014ቱ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ለአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን የተሰለፈው ፔሬዝ የፍጹም ቅጣት ምት መምቻ ነጥቧን እንደ ማንጸሪያ ይጠቀማት እንደነበር ተናግሯል፡፡

በጨዋታው የመጨረሻ ምዕራፍ ኬልቪን ኦሶሪዮ ጎል ቢያስቆጥርበትም ሪቨርፕሌት ጨዋታውን በድል በማጠናቀቁ የምድቡ መሪ ሆኗል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአቤል ጀቤሳ
ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *