የኒዮርክ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የትራምፕን ድርጅት “በወንጀል ደረጃ” እያጣራ መሆኑን ገልጿል ፡፡

የከተማዋ ከፍተኛ አቃቤ ህግ ቃል አቀባይ ሌቲያ ጄምስ በዶናልድ ትራምፕ ንብረት በሆነው ኩባንያ ላይ የተደረገው ምርመራ “ከእንግዲህ ሲቪል (የተለመደ ) ብቻ አይደለም” ብለዋል ፡፡

ትራንፕ ስልጣኑን ከመረከባቸው በፊት የቀድሞው የሪፐብሊካን ፕሬዝዳንት የገንዘብ አያያዝን በመመርመር ላይ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ ትላንት ረቡዕ ዕለት ምንም ዓይነት ጥፋት አለመፈጸማቸውን ክደው ተከራክረዋል “በግድ የወንጀል ፍለጋ ላይ ናቸው” ሲሉ ተችተዋል ፡፡

የአቃቤ ህግ ቃል አቀባይ ፋቢየን ሌቪ ማክሰኞ ለቢቢሲ እንደተናገሩት “በድርጅቱ ላይ ያደረግነው ምርመራ ከእንግዲህ የተለመደ ብቻ አለመሆኑን ለትራምፕ ድርጅት አሳውቀናል ፡፡

አሁን ከማንሃንታን ዳ ጋር በመሆን የትራምፕ ድርጅትን በወንጀል ደረጃ በንቃት እየመረመርን ነው ተጨማሪ አስተያየት የለንም ብለዋል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *