ቅናሽ ስለመደረጉ ግልጽ በሆነ መንገድ ያላሳወቁ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን አስጠነቀቀ

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አልባሳት ና የኤሌክትሮኒክስ መሸጫ ሱቆች ውስጥ ታላቅ ቅናሽ የሚል ጽሁፍ ብቻ በመለጠፈ ነገር ግን ስለቅናሹ ግልጽ በሆነ መንገድ ለሸማቹ ማህረሰብ በማያሳውቁ የንግድ ተቋማት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ትክክለኛ ቅናሽ መሆኑንም ከቀደመው ዋጋ አንጻር ማወቅ በማይቻልበት ሁኔታ የተጻፉ መሆናቸውን እንዲሁም በትክክል በየትኞቹ እቃዎች ላይ ቅናሽ ስለመደረጉ የማያሳውቁ ሆነው እንዳገኙዋቸው በክትትል ወቅት ማየታቸውን የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን አቤቱታ ምርመራ እና ክስ አቀራረብ ዳይሬክተር አቶ ጌትነት አሸናፊ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

እንዲህ ያለው የማስታወቂያ ሂደት በንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን መመሪያ መሰረት አሳሳች ተብሎ በመቀመጡ ተቀባይነት የለውም ብለዋል አቶ ጌትነት፡፡

እንዲህ አይነት ሁኔታ በተለይ አልባሳት ና የኤሌክትሮኒክስ መሸጫ ሱቆች እንደሚስተዋል እና በብዛት በበአላት ወቅት ቁጥራቸው እንደሚጨምር አንስተዋል፡፡

50 በመቶ ቅናሽ እና መሰል የሚሉ ማስታወቂያዎች በመለጠፍም ህብረተሰቡን ሊያታልሉ አይገባም ተብሏል

ሸማቹ ወደ ግብይት ሲወጣም ህጋዊ ነጋዴ መሆኑን ማወቅ አለበት ይህም ከህገወጥ ተግባር እንዲጠበቅ ያደርገዋል ሲሉ አቶ ጌትነት ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
መቅደላዊት ደረጄ
ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *