የአሜሪካ እገዳ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ቢጎዳም ቀዩ መስመር ግን የኢትዮጵያ ነፃነት በገንዘብ ሊቀየር የሚችል አለመሆኑን የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገለጸ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ዙሪያ በሰጡት መግለጫ፣ የአገር ነፃነት በገንዘብ አይለወጥም ብለዋል።

ወቅታዊዉ የአሜሪካ ውሳኔ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ቢያደርስም፣ ነገር ግን ለገንዘብ ተብሎ ኢትዮጵያ ነፃነቷን አሳልፋ አትሰጥም፤ ይሄ ቀይ መስመር ነው ብለዋል ቃል አቀባዩ።

መንግስት ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለሚያገኘው ገንዘብ ብሎ ልደራደር ቢል እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን በገንዘብ የሚቀይር አይደለም ነው ያሉት።

የአሜሪካ እገዳ የሁለቱን አገራት ግንኙነት የሚጎዳ ብቻም ሳይሆን፣ ቀጠናውና ሌሎች አገራት ላይም ተፅዕኖ የሚያሳድር በመሆኑ አሜሪካ ውሳኔዋን ደግማ ልታስብበት ይገባልም ተብሏል።

የአሜሪካ ውሳኔ በኢትዮጵያ ላይ የኢኮኖሚ ተፅዕኖ ቢኖረውም የኢትዮጵያ ሉአላዊነት ግን ለሚደራደር የሚቀርብ አይሆንም ሲሉ አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *