ስፖርት

ዚዳን ከማድሪድ ተለያየ

ሪያል ማድሪድ በዚህ የውድድር ዘመን አንድም ዋንጫ አላሸነፈም፡፡

የከተማ ተቀናቃኙ አትሌቲኮ ማድሪድ የላ ሊጋውን ዋንጫ ማንሳቱ ደግሞ የደጋፊዎቹን ብስጭት የበለጠ ከፍ አድርጎታል፡፡

ሪያል ማድሪድ ባወጣው መግለጫ የዚዳንን ውሳኔ ‹‹የግድ ማክበር ይኖርብናል›› ብሏል፡፡

ክለቡ የ48 ዓመቱን ዚዳን ‹‹ድንቅ ፕሮፌሽናል ፣ ለስራው የተሰጠ እና ስራውን የሚወድድ›› መሆኑን በመግለጽ አመስግኖታል፡፡

በማድሪድ በቆየባቸው ዓመታት ያበረከተውን አስተዋጽኦም አድንቋል፡፡

የቀድሞው የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ከ2001 እስከ 2006 ድረስ ለሪያል ማድሪድ ተጫውቷል፡፡

በክለቡ በአሰልጣኝነት ባሳለፈበት የመጀመሪያ ዘመን ቆይታው ከ2016 እስከ 2018 ሶስት የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን በተከታታይ አንስቷል የላ ሊጋ አሸናፊም ሆኗል፡፡

ከክለቡ ከተለያየ ከ10 ወራት በኋላ ዳግም ተመልሶ ሃላፊነቱን ከተረከበ በኋላ ሁለተኛ የላ ሊጋ ዋንጫውን ባለፈው የውድድር ዘመን አሳክቷል፡፡

አቤል ጀቤሳ
ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *