በሰሜን ምስራቅ ሪጅን የሚገኙ 7 ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያድርግ የ 4ጂ ኤልቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል

ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ምስራቅ ሪጅን የሚገኙ 7 ከተሞችን የአራተኛው ትውልድ ኢንተርኔት አገልግሎት በዛሬው ዕለት በደሴ ከተማ አስጀምሯል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ፣ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ይህ አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ 5 መቶ 77ሺህ ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል ።

አገልግሎቱ የተጀመረባቸው ከተሞችም፣ ደሴ፣ኮምቦልቻ ፣ወልዲያ፣ከሚሴ፣ላሊበላ፣ ቆቦና ሃይቅ ናቸው።

የአገልግሎቱ መጀመር፣ ደንበኞች ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያስችልም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አገልግሎቱ ደንበኞች የኦንላይን ግብይት እና ሌሎች የመረጃ ልውውጥ ማድረግ ያስችላል ተብሏል።

ድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
አባቱ መረቀ
ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.