በዘንድሮው ዓመት በሚደረገው ምርጫ ላይ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለ 6 ነጥብ የሰብአዊ መብት አጀንዳዎች ላይ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ።

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በዛሬው እለት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ባካሄደው ስብሰባ ላይ እንዳለው ፖለቲካ ፓርቲዎች ባለ 6 ነጥብ የሰብአዊ መብት አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ፓርቲዎቹ ምርጫውን ካሸነፉ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲከሰት ምን ተጨባጭ እርምጃ እንደሚወስዱ ጭምር ማካተት ይገባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ በዋናነት ከህገ መንግስት ማሻሻያ አንስቶ አዳዲስ ኢትዮጲያ ልትቀበላቸው የሚገቡ ህጎች እና ድንጋጌዎችን ካሉ በመፈተሽ ለሰብአዊ መብት ጥሰት ክፍተት የፈጠሩትን ድንጋጌዎችን ጭምር ለማስተካከል ያላቸውን አቋም በማኒፌስቷቸው ጭምር ተካትቶ ማየት እንፈልጋለን ብለዋል።

በኮሚሽኑ ባለ ስድስት ነጥብ አጀንዳዎች ተብለው የመጡት “ተጨባጭ የሰብአዊ መብቶች እርምጃ ቃልኪዳን፤ ለሰብአዊ መብቶች በቁርጠኝነት መቆም፤ ምርጫው ለስርአተ ፆታ ምላሽ ሰጪ መሆኑን ማረጋገጥ፤ የህግ እና የፖሊሲዎች ማሻሻያ ቃል ኪዳን ፣ የመንቀሳቀስ፣ የመደራጀት፣ መረጃ የማግኘት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ማረጋገጥ፤ ከግጭት ቀስቃሽ እና የጥላቻ ንግግር እንዲሁም ከሀይል እርምጃ ሙሉ በሙሉ መቆጠብ ” የሚሉት ናቸዉ።

በተጨባጭ ገዢው ፖርቲ እዚህ ላይ ፍላጎት ማሳየት ይጠበቅበታል ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.