ቱሪዝም ኢትዮጵያ‹ የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት ( land of origin) › አምባሳደር እየመለመልኩ ነው አለ፡፡

ቱሪዝም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ በነበረበው የህግ ማስከበር ዘመቻ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ የተፈጠረውን የእይታ ችግር ለማስተካከል ያግዘኝ ዘንድ የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት አምባሳደር እየመለመልኩ ነው ብሏል፡፡

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ስለሺ ግርማ እንደተናገሩት፣ ለቱሪስት አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት ያሉንን የቱሪዝም ሀብቶች ማስተዋወቅና የተፈጠረውን የእይታ ችግር የገጽታ ግንባታ ስራ በመስራት ማስተካከል ዋነኛ አላማችን አድርገን እየሰራ እንገኛለን ብለዋል፡፡

የማስተዋወቁን ስራ አሁን ላይ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አሁን ደግሞ በተለያዩ የአለም ሀገራት ያሉ ዜጎቻችንን በመጠቀምና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት(land of origin) አምባሳደር እየመለመልን ነው ብሏል ድርጅቱ፡፡

በአምባሳደርነት የሚመረጡት ሰዎች በተለያዩ የስራ ዘርፍ ላይ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መሆናቸዉንም ድርጅቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ይህን ለማስፈጸምም መስፈርቱንና አስፈላጊነቱን ለሁሉም አምባሳደሮች ቱሪዝም ኢትዮጵያ ስልጠና መስጠቱን ዋና ስራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል፡፡

በመቅደላዊት ደረጀ
ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *