ኢስሃቅ ሄርዞግ የእስራኤል ፕሬዝዳንት ሆነዉ ተመረጡ

በእስራኤል ፖለቲካ ዉስጥ ስማቸዉ በቀዳሚነት የሚቀመጠዉ ኢስሃቅ ሄርዞግ የወቅቱን ፕሬዝዳንት ሪዉቨሊንን በመተካት ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ታውቋል፡፡

ሄርዞግ ማሪያም ፔሬትዝን በቀላሉ በማሸነፍ እንደተመረጡም ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

የ60 አመቱ ኢስሃቅ ሄርዞግ፤ የሁሉም ፕሬዝደንት ሆኜ ህዝቤን ለማገልገል እሰራለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁም የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት ማስተላለፋቸዉ ተሰምቷል፡፡

እስራኤል በሁለት አመት ዉስጥ 4 ምርጫዎችን ብታካሂድም ምርጫዉን በበላይነት ያሸነፈ ፓርቲ ባለመኖሩ አገሪቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት ዉስጥ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያም ኔታንያሁም የጥምር መንግስት እንዲመሰርቱ የተሰጣቸዉ የጊዜ ገደብ ዛሬ ምሽት መጠናቀቁን ተከትሎ ከተፎካካሪዎቻቸዉ እልህ አስጨራሽ ትግል እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
አባቱ መረቀ
ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *