የቀድሞው የግብጽ አምባሳደር መንግስት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የያዘውን አቋም በመተቸታቸው ለእስር ተዳረጉ

ግብጽ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የአል-ሲስ መንግስት የያዘውን አቋም ተችተዋል ያለቻቸውን አንድ የቀድሞው ዲፕሎማቷን ማሰሯ ተሰማ፡፡

በቬንዙዌላ የካይሮ አምባሳደር ሆነው ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉት የያህ ናጅም ቤተሰቦች እንደተናገሩት የፀጥታ ኃይሎች በመኖሪያ ቤታቸው ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉዋቸው እና ከዚያም በኋላ ለሦስት ቀናት የደረሱበት አለመታወቁን ገልጸዋል፡፡

ኒው አረብ ለነጅም ቅርብ የሆኑ ምንጮችን በመጥቀስ እንደዘገበው አቃቤ ህግ “ከሽብርተኛ ቡድን ጋር በመቀላቀል ፣ የሐሰት ዜና በማሰራጨት እና ማህበራዊ ሚዲያዎችን ያለአግባብ በመጠቀም በሚል ” ክስ እንደመሰረተባቸው ተገልጿል።

ምርመራ እስኪጀመር ድረስ ግን የ 15 ቀናት እስራት እንደተፈረደባቸው ዘግቧል ፡፡

ቤተሰቦቻቸውም ከምርመራው በኋላ መንግስት “የግብፅን ህግ በግልፅ በመጣስ” ወደማይታወቅ ስፍራ አዘዋውሯቸዋል ብለዋል ፡፡

ጨምረው ሲገልጹም “ለዓመታት እንደ ዲፕሎማት ሆነው ሀገራቸውን አገልግለዋል” የታሰሩበት ምክንያትም ቢሆን “የትውልድ አገሩን ለመከላከል ለነፃነቱ የከፈለው ዋጋ” እንደሆነ እናምናለን ብለዋል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *