ቤጂንግ ለዋሽንግተን ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን፣ ዋሽንግተን ከታይዋን ጋር ማንኛውንም ዓይነት ይፋዊ የሆነ ግንኙነትን እንድታቆም አሳስበዋል፡፡

ዋሽንግተን ከታይዋን ጋር እያደረገችው ካለው የተሳሳተ አካሄድ እንድትቆጠብም ቤጂንግ አስጠንቅቃለች፡፡

ሚኒስቴሩ ይህን ያለው የአሜሪካ የህግ አውጭዎች ልዑካን ቡድን ወደ ታይፒ ደሴት በመምጣት ዋሽንግተን 750,000 የኮሮናቫይረስ ክትባት ለመለገስ ቃል መግባቷን ማስታወቋን ተከትሎ ነው፡፡

ቤጂንግ ለደሴቲቱ የራሷ ምርት የሆነውን የሲኖፋርም ክትባት አቅርባለች፣ ነገር ግን በታይፒ ያለው መንግሥት ለደህንነታቸው ስጋት እንዳላቸው በመግለጽ ከውጭ እንዲገባ ፈቃድ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡

የአሜሪካ የልዑካን ቡድንም የማንንም ፍቃድ ሳይጠይቅ ደሴቲቱን መጎብኘቱ በቻይና ቁጣን አስነስቷል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሌንከን ከታይፔይ ጋር የንግድ ስምምነት ለመጀመር ስለታቀደው አወዛጋቢ አስተያየታቸውም ጉዳዪን አባብሶታል ፡፡

ይህ ብቻም ሳይሆን ብሊንከን በዋሽንግተን በተካሄደው የምክር ቤት ስብሰባ ከታይዋን ጋር የተለያዩ ውይይቶች እንደሚካሄዱ አስታውቀዋል፡፡

ብሊንከን ታይዋን እራሷን ለመከላከል የሚያስችል አቅም ሊኖራት ይገባል፤ ዋሽንግተንም ለዚሁ ዓላማ የሚውሉ ከፍተኛ የመሣሪያ ሽያጭን ማቅረቧን ትቀጥላለች ማለታቸዉን ፕረስ ቲቪ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
ሰኔ 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *