በአይ.ሲ.ቲ ችግር ምክንያት 60 ለሚሆኑ የምርጫ ክልሎች መታተም የነበረባቸው የድምጽ መስጫ ሰነዶች አልታተሙም – ምርጫ ቦርድ

60 ለሚሆኑ የምርጫ ክልሎች መታተም የነበረባቸው የድምጽ መስጫ ሰነዶች በአይ.ሲ.ቲ ቴክኖሎጂ ችግር ምክንያት አለመታተማቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ችግሩን ለመፍታት አማራጭ የህትመት ስራዎች በአፋጣኝ ተሰርተው ምርጫው በተቆረጠለት የጊዜ ሰሌዳ ሰኔ 14 እንደሚካሄድም የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ችግሩ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በአይ.ሲ.ቲ ለማዘመን በሚሰራው አድካሚ ስራ ላይ የተፈጠረ እንደሆነ እና መንስኤውም ተጣርቶ ይፋ እንደሚደረግ ሰብሳቢዋ ገልፀዋል፡፡

በመግለጫው ላይ የተገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም የምርጫ ቦርድ የተፈጠረውን ችግር በግልፀኝነትና በሃላፊነት በመውሰድ ማሳወቅ መቻሉን በማመስገን ለመፍትሄ እርምጃው መሳካት ከቦርዱ ጎን በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጡም አስታውቀዋል፡፡

ቦርዱ በመግለጫው ወቅት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ላነሷቸው ሌሎች ተጨማሪ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *