የኤርትራ ወታደሮች መቼ ከትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ ለቀው እንደሚወጡ መረጃው የለኝም ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።

በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት በተፈጠረው ክፍተት ወደ ክልሉ ገብተው የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች መውጣት መጀመራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሆኖም ሙሉ ለሙሉ ክልሉን ለቀው መቼ እንደሚወጡ በውል የተቆረጠ ቀን አለመቀመጡን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፣በጉዳዩ ላይ ከሰሞኑ ከመከላከያ ሃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉን አንስተው የኤርትራ ወታደሮች መውጣት መጀመራቸውን ከአመራሮቹ ሰምተናል ብለዋል ።

ይሁን እንጂ ወታደሮቹ መቼ ሙሉ በሙሉ ክልሉን ለቀው እንደሚወጡ መረጃው የለኝም ነው ያሉት አምባሳደር ዲና።

መንግስት ሕግ ማስከበር ባለው ዘመቻ ምክንያት ወደ ትግራይ ክልል የገቡት የኤርትራ ወታደሮች እንደሚወጡ የሁለቱ አገራት መሪዎች ስምምነት ላይ ስለመድረሳቸው መናገራቸው የሚታወስ ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
አባቱ መረቀ
ሰኔ 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *