ኢትዮ-ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

የገንዘብ ሚኒስቴር እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ኤጀንሲ እንዲሁም የኢትዮ-ቴሌኮም የቦርድ አመራር በተገኙበት ኢትዮ-ቴሌኮም በከፊል ወደ ግል ይዞታ የማዘዋወር ምዕራፍ የተጠናቀቀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም እ.ኤ.አ በ2018 የመንግስት ልማት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል ይዞታ የማዞር አንዱ አካል የሆነው የኢትዮ ቴሌኮም የ40% ድርሻ ለመሸጥ በሂደቱ ተሳተፊ የሚፈልጉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎች የፍላጎት መግለጫ Expression of Interest (EOI) ከነገ ሰኔ 08 ቀን 2013 ጀምሮ ማስገባት እንደሚችሉ የኢትዮጵያ መንግስት አሳውቋል፡፡

የፍላጎት መግለጫው ለአንድ ወር የሚቆይና ዝርዝሩም በገንዘብ ሚኒስቴር እና በመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ እንደሚለቀቅ አቶ ዝናቡ ይርጋ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡

ፍላጎት መግለጫው ለሰላሳ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ተወዳዳሪ ባለሀብቶችን በአፍሪካ ትልቁ በሆነው የኢትዮ-በከፊል በማዛወር ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀረቦላቸዋል፡፡

ሂደቱን የዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን ከግንዘቤ ያስገባ ከመሆኑ ባለፈ በፋይናንስ፣ በንግድ ሥራ ዕቅድ ፣ በሕግ እና ታክስ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን በሚመለከት ያሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራን በተመለከተ በማማከር ረገድ ዴሎይት እንደ ዋና የግብይት አማካሪ ሆኖ የሚሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የመወዳደሪያ ፍላጎት መግለጫውን ተከትሎ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዕቅድ ጥያቄያቸውን (Request for Proposal (RFP)) የሚያስገቡ ሲሆን ይህም አጠቃላይ ሂደቱ ወቅቱን የጠበቀ፣ ቀልጣፋ እና የተስተካከለ አሰራርን በመያዝ የሚገለጽ እንደሆነ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በላከልን መግለጫ አስታውቋል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

የኢትዮጵያዊያንሰኔ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *