የሞጆ መቂ-ባቱ መንገድን ለተሸከርካሪ ክፍት ለማድረግ፣ የቀሩት የክፍያ ጣቢያዎች ገጠማ ግንባታ መሆኑንና ገጠማውን የማከናወኑ ስራ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ከ አንድ ወር በኋላ ለትራፊክ ክፍት እንደሚደረግ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡
በመንገዱ የተቀሩት ስራዎች የክፍያ ሲስተሙን ለማስጀመር የሚረዱ ገጠማዎችን ማጠናቀቅና፣ ለክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ማስረከብ ብቻ መሆኑን የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መሃንዲስ የሆኑት ኤሊያስ ግርማ ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቀዋል፡፡
መንገዱ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ በቀን ከ 4 እስከ 5 ሺ በላይ ተሸከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለውም የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ ነግረውናል፡፡
92 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው እና የሞጆ-ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው የሞጆ-ባቱ የመጀመሪያ ምእራፍ የፍጥነት መንገድ፣ ግንባታው ተጠናቆ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ አማካኝነት መመረቁ ይታወሳል፡፡
በየውልሰው ገዝሙ
ሰኔ 09 ቀን 2013 ዓ.ም
