በሰሜን ኮሪያ አንድ ኪሎ ሙዝ 45 ዶላር እየተሸጠ እንደሆነ ተነገረ

ባለፈው አመት የተከሰተው የታይፉን አውሎ ንፋስ ከፍተኛ ጎርፍ በማስከተሉ አገሪቱ በግብርናው ዘርፍ በቂ የእህል ምርት ማምረት አለመቻሉን ተከትሎ ሀገሪቱ የምግብ እጥረት እንደገጠማት አስታውቃለች፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ከሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በነበራቸው ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት “የህዝቡ የምግብ ሁኔታ አሁን እየተወሳሰበ ነው” ፣ ሀገሪቱ የምግብ እጥረት ገጥሟታል ብለዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ አንድ ኪሎ ሙዝ 45 ዶላር እየተሸጠ እንደሚገኝ ኤንኬ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በኑክሌር መርሃግብሯ ምክንያት ከተጣለባት ዓለም አቀፍ ማዕቀቦች ጋር እየታገለች ቢሆንም ብሔራዊ የኢንዱስትሪ ምርት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ 25 በመቶ አድጓል ብለዋል ፡፡

በሚያዝያ ወር ላይ ኪም አገራቸው አርዱስ ማርች ተብሎ እንደሚጠራው ረሃብ እንዳያጋጥማት እና ህዝባችንን ልንረዳ ይገባል ብለው ነበር።

አርዱስ ማርች ተብሎ የሚታወቀው በሰሜን ኮሪያ ክፉ የረሃብ ዘመን ሲሆን ይህም በአውሮፓውያኑ 1990 ወቅት ነው።

በወቅቱ በረሃብ የሞቱ ሰሜን ኮሪያውያን ቁጥር በትክክል ባይታወቅም እስከ 3 ሚሊዮን ይገመታል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *