በእንጦጦ ኬላ ባለው ፍተሻ የተነሳ የትራፊክ መጨናነቅ ተከስቷል

በእንጦጦ ኬላ እየተከናወነ በሚገኘው ፍተሻ ምክንያት ፣ ከሱሉልታ ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ላይ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ተፈጥሯል።

ይህንንም ተከትሎ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡና ከአዲስ አበባ የሚወጡ መንገደኞች ከፍተኛ መጉላላት እንደገጠማቸው ኢትዮ ኤፍ ኤም በቦታው ተገኝቶ ታዝቧል።

ኬላ ላይ የሚደረገው ፍተሻ ከዛሬ ጠዋት ማለዳ ጀምሮ እየተከናወነ ያለ ሲሆን ተማሪዎችን ጨምሮ በርካታ መንገደኞች ወደ አዲስ አበባ በእግራቸው እየተጓዙ መሆናቸውን ታዝበናል።

“መስመሩ አማራጭ መንገድ ስለሌለው እንዲህ አይነት ፍተሻ፣ እንዲሁም የትራፊክ አደጋ ሲከሰት ለከፍተኛ መጉላላት ይደርስብናል “ ሲሉ በቦታው የነበሩ አሽከርካሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

አባቱ መረቀ
ሰኔ 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *