የሩሲያ ቅጥረኞች ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ መውጣት አለባቸው ሲል የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት አሳሰበ፡፡

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የሩሲያ የግል የፀጥታ ኃይሎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጥምረቱ ከአማፅያን ጋር በሚደረግ ውግያ ወቅት የሩሲያ ቅጥረኞች በዜጎች ላይ በደል ይፈጽማሉ ማለቱን ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል።

እናም አሁን በሩስያውያን ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰልፎችን እያቀናጀሁ ነው ብሏል ጥምረቱ፡፡

ከሰሞኑ አማጺያን በሰሜን ምስራቅ ሀውቲ-ኮቶ ክልል 10 ሰዎችን ገድለው ቤቶችን አቃጥለዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

ሩሲያውያን በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከፀጥታ ኃይሎች ጎን ለጎን ሥልጠናና ውጊያ እንደሚያደርጉም ተገልጿል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ የግል የፀጥታ ኃይሎች በቅርቡ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸዉን ሪፖርቶች ደርሰውኛል ማለቱ ይታወሳል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.