ኢዜማ ሰኔ 14 ቀን 2013 የተደረገው 6ኛው አገራዊ ምርጫ ሂደቱ እና ውጤቱ ሙሉ በሙሉ ለሕዝብ የተገለፀ ባይሆንም በብዙ ችግሮች የታጀበ ነበር ብሏል፡፡

ፓርቲው ለዚህ ምርጫ ሰላማዊነትና የአገሪቱን የነገን ቀጣይነት በምርጫ ለማረጋገጥ፣ ዜጎች በምርጫው ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ኢዜማ የበኩሉን ድርሻ በኃላፊነት መውጣቱን አስታዉቋል፡፡

ፓርቲው ከምንም በላይ ለአገር መረጋጋትና ለሕዝብ ሰላም ያለውን ቁርጠኝነትም በተግባር አስመስክሯል ነዉ ያለዉ፡፡

በምርጫ ወቅት ኢዜማ በተወዳደረባቸው በርካታ የምርጫ ክልሎች ያጋጠሙትንና በየሰዓቱ ለምርጫ ቦርድ ያሳወቅናቸው በርካታ ችግሮችን በአጽንኦት ተመልክቶ ውሳኔ የማይሰጥባቸው ከሆነ ጉዳዩን ወደ ፍትህ አካላት እንደሚያቀርበውም ጠቁሟል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዉ ሰላማዊ ትግል ቀጣይነት ያለውና ከምርጫ በኋላም ቢሆን ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዚህ ረገድ ኢዜማ ጊዜያዊ ፓርቲ ሳይሆን ገና ከመነሻው ከምርጫ ወረዳ ጀምሮ የተዋቀረ በመሆኑ ሩቅ ተጓዥና ዘመን ተሻጋሪ ፓርቲ ሆኖ ይቀጥላልም ተብሏል፡፡

ከዚህ አንጻር በምርጫው ሒደት ያጋጠሙ ችግሮችን በሕግ አግባብ እየጠየቀ ከዚህ ምርጫ ማግስት ጀምሮ የድርጅቱን መዋቅር ይበልጥ በማጠናከር ወደ ሥራ መግባቱንም ፓርቲዉ ገልጿል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *