“ምርጫ ፍትህና ዲሞክራሲን ሊያመጣ አይችልም” ሲል ኦፌኮ ተናገረ፡፡

6ተኛዉ አገራዊ ምርጫ መካሄዱን ተከትሎ መግለጫ ያወጣው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ ”በብሔራዊ ድርድር ያልተደገፈ ምርጫ የፖለቲካ ቲያትር ከመሆን በዘለለ ፍትህና ዲሞክራሲን ሊያመጣ አይችም” ብሏል፡፡

ፓርቲው በማህበራዊ የፌስቡክ ገጹ እንዳስነበበው ለሶስት አመታት ያህል በሀገሪቱ ስኬታማ የዴሞክራሲ ሽግግር እንዲደረግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር አስታውሶ ነገር ግን የፓለቲካው መሪዎች ትርፋማው ውይይት እንዳይደረግ ሲገፉ እንደነበር ተናግሯል፡፡

የእኛ ፍላጎትም ሆነ ሲሰሙ የነበሩ ድምጾች ምርጫው ከውይይት በኃላ እንዲደረግ የሚጠይቁ ነበሩ፤ይህንንም አረጋግጠናል ሲልም ያክላል፡፡

ምርጫ ለሌላ ጊዜ ተላልፎ መላው ኢትዮጵያንን የሚወክል እንዲሆን እንዲደረግ አስቀድሞ ሲጠይቅ መቆየቱንም ነዉ የገለጸዉ፡፡

በጥልቀት ከተመለከትነው የመራጮች ፍላጎት አሁንም በጠረጴዛ ላይ ይገኛል ብሏል ኦፌኮ በመግለጫው፡፡

ምርጫ ቦርድ እንዳስታወቀው ከምርጫ ቦርድ ውጭ 79 የምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተዋል፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ ድምጾች ምርጫው በጭራሽ ያልተደረገባቸው ናቸው ፡፡

በኦሮሚያ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወረዳዎች የብልጽግና ፓርቲ ድራማውን ለማስጌጥ ከራሱ ጋር ተወዳድሯል ብሏል ኦፌኮ፡፡

በጦርነት ምክንያት ትግራይ ውስጥ ምርጫ የለም፤ከ 100 እጅ በድምሩ በሃምሳ በመቶው ያህሉ ማለት ይቻላል ምርጫ አልተደረገም፤ ተጽዕኖውንም ለመተንበይ የፓርቲ ሰው መሆን አያስፈልገውም ብሏል፡፡

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና ፌዴራል ኮንግረስ ከምርጫው ተገፍተን መውጣታችን ማንንም አልጠቀመም ነዉ ያለዉ፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ለለውጡ ትልቅ መስዋትነት ከፍሏል ግን ክህደት ተፈጽሞበታል ነው ያለው ኦፌኮ፡፡

ምርጫ በአገሪቱ ውስጥ በፍላጎት የተሞላ መሆን ካልቻለ ለሁሉም ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ፣ ሰላምን እና መረጋጋትን እና አንድነትን ሊያመጣ አይችልም፤ብልጽግናን ሊያመጣ አይችልም ብሏል ኦፌኮ በመግለጫው ፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *