በነሐሴ በዛምቢያ በሚደረገው አጠቃላይ ምርጫ፤ በሶስት የምርጫ ክልሎች ምርጫው ተሰረዘእንደ አውሮፓውያኑ ነሐሴ 12 2021 ዛምቢያ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ ታደርጋለች፡፡

በዚህ ቀን በሶስት የምርጫ ክልሎች ላይ ለፓርላማ የሚደረገው ምርጫ አይከናወንም ተብሏል፡፡ ምርጫው የማይደረገው በተጠቀሱት የምርጫ ክልሎች ላይ አንዱ የፓርላማ እጩ ተወዳዳሪ በመሞቱና ሁለቱ ደግሞ ከውድድሩ ራሳቸውን በማግለላቸው ነው፡፡

እንደ ዛምቢያ ህገ መንግስት የምርጫ እጩ ተወዳዳሪ ከሞተ ወይም ራሱን ካገለለ በአዲስ መልክ ሌላ እጩ ይተካል እንጂ ከሞተው ወይም ራሱን ካገለለው እጩ ውጪ ምርጫው አይደረግም፡፡

የዛምቢያ የምርጫ ኮሚሽንም አዲስ እጩ እንዲተካ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በሶስቱ ክልሎች ላይ ነሐሴ 12 ምርጫ አይደረግም ብሏል፡፡

ከሶስቱ የምርጫ ክልሎች ውስጥ ማንዴቩ እጩው የሞተበት የምርጫ ክልል ሲሆን፣ ማዕከላዊ ሉሳካ( Lusaka Central) እና ምፑሉንጉ ደግሞ እጩዎቹ ከውድድር ራሳቸውን ያገለሉባቸው የምርጫ ክልሎች ናቸው፡፡ከማዕከላዊ ሉሳካ (Lusaka Central) ራሳቸውን ከምርጫ ያገለሉት ዕጩ ተወዳዳሪ ለገዢው ፓርቲ Patriotic Front party የሚወዳደሩ ነበሩ፡፡

ቢቢሲውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ። ድረ ገጻችንን

ሄኖክ አስራት

ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *