የቶታል ኩባንያ ስያሜውን ወደ ቶታል ኢነርጂስ ቀየረየፈረንሳዩ የነዳጅ ኩባንያ ባለአክሲዮኖች ኩባያውን ወደ ሁለገብ የኢነርጂ ኩባንያነት ለመለወጥ ለሚያደረገው ስትራቴጂካዊ ሒደት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል ያለውን ውሳኔ ከዋና መስሪያ ቤቱ ፓሪስ ማሳለፉ ተሰምቷል፡፡
በባለአክሲዮኖች ስብሰባው ላይ የቶታልኢነርጂስ ሊቀመንበር እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚስተር ፓትሪክ ፑያኔ “ኃይል ሕይወት ነው፡፡
የእድገት ምንጭ ስለሆነ ሁላችንም እንፈልገዋለን “ ብለው ተናግረዋል፡፡
“ ዛሬ የአየር ንብረት ፈተና ላጋጠማት ምድራችን ዘላቂ የሆነ የልማት አስተዋፅዖ ለማድረግ ወደ አዲስ የኃይል አማራጮች በአንድነት ወደ ፊት እየሄድን ነው ብለዋል፡፡
“የኃይል አማራጮች በሒደት እየተሻሻሉ መምጣታቸው ወሳኝ የኃይል ሽግግር ጉዞ በመሆኑ፣ ይህንን ሽግግር ለማሳካት የቶታል ወደ ቶታል ኢነርጂስ መለወጥ እውን ሆኗል“ ብለዋል፡፡
አዲሱ ስያሜ እና የንግድ ምልክት ቶታል ኢነርጂስ አስተማማኝ እና ንፁህ የሆነ ሀይል ለማመንጨት እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ለማቅረብ ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ገልጿል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም











