በትግራይ ክልል የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት በጎ እርምጃ መሆኑን የአሜሪካ መንግስት አስታወቀ ፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳስታወቀው መንግስት በትግራይ ክልል የተኩስ አቁም ስምምነት ውሳኔ መወሰኑ ጥሩ እርምጃ ነው ብሏል።

በክልሉ ያለውን ችግር ለመፍታትም ሁሉም አካላት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ።

ጉዳዩን የአገሪቱ መንግስት በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ያነሳው መግለጫው፣ ሁሉም ወገኖች ለሰብዓዊ ዕርዳታ ሰጪ ተቋማት ምቹ ሁኔታን መፍጠር አለባቸው ነው ያለው።የአሜሪካ መንግስት የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብ ከኢትዮጵያ መንግስት፣ ከክልሉ ሃላፊዎች እና ከተባበሩት መንግስታት ጋር በቅንጅት ይሰራልም ነው ያለው ኤምባሲው።

ከዚህ በተጨማሪም የተኩስ አቁም ስምምነቱ ውጤታማ እንዲሆን የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል በአስቸኳይ እንዲወጡ ተጠይቋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ መንግስት በክልሉ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት እንዲያስጀምርና ለዕርዳታ ሰጪ አካላት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ የአሜሪካ መንግስት ጥሪውን አቅርቧል።

የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተከትሎ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል ወጥተው በድንበር ላይ መስፈራቸው ተነግሯል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *