በካናዳ የሙቀት መጠኑ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

በካናዳ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የሙቀት መጠኑ የጨመረ ሲሆን በዚህም በካናዳ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ ሳቢያ ህይወታቸው ሊያልፍ መቻሉ ተነግሯል፡፡

የካናዳ ምእራባዊ ግዛት በሆነችው ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ውስጥ የሙቀት መጠኑ 121 ዲግሪ ፍራናይት ወይንም 49.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ሙቀት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በዚህም ካሳለፍነዉ ሰኞ ጀምሮ 70 የሚሆኑ ሰዎች በዚህ ሙቀት ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሟቾችም አዛውንቶች መሆናቸው ተነግሯል ፡፡

ከዚህ ሳምንት በፊት በካናዳ ያለው የሙቀት መጠን 45 ዲግሪ ሴልሺየስ ነበር፡፡

በቫንኩ-ቨር ዳርቻ በበርናቢ ከተማ የሚገኘው የካናዳ ፖሊስ ማይክ ካላንጅ እንዲህ ሲሉ አስጠንቅሰቀዋል፤ “የአካባቢው ዜጎች ጎረቤቶቻቸውንም መፈተሽ አለባቸዉ፣ የቤተሰብ አባላትን መመርመር እንዲሁም ሊያውቋቸው የሚችሏቸውን አዛውንቶች ሁኔታ መፈተሸ አለባቸዉ” ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

“ለዚህ የአየር ሁኔታ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰባችን አባላትም በተለይም ለአረጋውያን እና መሰረታዊ የጤና ችግሮች ላለባቸው ሰዎች ገዳይ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል ፡፡

እንደ ፖሊስ ገለጻ ከሆነ ሙቀቱ በበርን-ኩቢ እና በሱሬ በቫንኩ-ቨር መንደሮች ውስጥ ለ 69 ሰዎች ሞት ምክንያት እንደሆነ ይታመናል ፡፡

አብዛኛዎቹ አዛውንቶች ወይም መሠረታዊ የጤና ችግሮች እንደነበሩባቸውም ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ቢቢሲ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በየዉልሰዉ ገዝሙ

ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *