በወላይታ ሶዶ ከተማ በተደጋጋሚ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት እየተፈጸመ መሆኑ ተነገረ፡፡

በደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ በኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ ቋሚዎች (ታወሮች) ላይ ተደጋጋሚ ስርቆት እየተፈጸመ እንደሚገኝ ተነገረ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚፈጽመው ስርቆት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ነው የሚናገረው፡፡

በከተማው ሁለት ታወሮች መውደቃቸውና 20 የሚጠጉ ታወሮች ብረታቸው ተገንጥሎ መወሰዳቸውን ነው መስራቤቱ ያስታወቀው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ በሁምቦ ላሬ ቀበሌ ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓም በከፍተኛ ኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፍያ ታወርና ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የስርቆት ወንጀል በመፈፀሙ በአካባቢው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እስካሁን እንደተቋረጠ ነው የተናገሩት፡፡

የስርቆት ወንጀሉ የተፈፀመው ከወላይታ ሰብስቴሽን ተነስቶ ለሦስት የደቡብ ዞኖች አገልግሎት በሚሰጥ የኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ መስመር ላይ እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

አሁን ላይ የኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ መስመሩን ጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎችን ሳይጨምር 1.5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወጭ እንደሚጠይቅ ነው አቶ መላኩ ታዬ የነገሩን፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *