ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሶማሊያ በሚቀጥለው ጥቅምት 30 2013 ዓ.ም ላይ የተራዘመውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደምታከናውን ገልጻለች፡፡
በሀገሪቱ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ባካሄዱት ምክክር ላይ፣ በሀገሪቷ የተራዘመውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲከናወን ተስማምተዋል፡፡
ለወራቶች ያህል የተራዘመው የሀገሪቱ ምርጫ በሚቀጥለው ጥቅምት ወር ላይ እንዲደረግ ነው የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከስምምነት ላይ የደረሱት፡፡
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በቲዊተር ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ ምርጫው የሚደርግበት መርሀ ግብር ወደ ፊት እንደሚገለጽ አስታውቋል፡፡
የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሀመድ ሁሴን ሮቤሌ እንደተናገሩት፣ ምርጫው ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ፋርማጆ የስልጣን ጊዜያቸው ያበቃው ከወራቶች በፊት ቢሆንም እስካሁን ድረስ በሀላፊነት ላይ ይገኛሉ፡፡
ይህንንም ተከትሎ ነበር በሀገሪቱ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመንግስት ጋር ግጭት ውስጥ የገቡት፡፡
ላለፉት ወራቶች በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች እና በመንግስት ደጋፊዎች መካከል ውጥረት ነግሶ ቆይቷል፡፡
የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የአውሮፓ ህብረት እንደዚሁም አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት በሀገሪቱ የተራዘመውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ባስቸኳይ እንዲደረግ ግፊት ሲያደርጉ መቆየታቸዉ አይዘነጋም፡፡
በመሆኑም በሚቀጥለው ጥቅምት 30 ሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫዋን ታደርጋለች ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡
አልጀዚራ
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም
