በ2014 በጀት ዓመት በክልል የተለያዩ ከተሞች የዳቦ ፋብሪካዎች ስራ ለማስጀመር ዝግጅት ተጠናቋል ተባለ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እንዳሉት፣በደሴ፣ሶዶ፣ነቀምት እና በሌሎችም የክልሎች ዋና ዋና ከተሞች የዳቦ ፋብሪካዎች እንደሚገነቡ ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካዎቹ ከሀገር ዉስጥ ባለሃብቶች እና ከዉጭ መንግስተት ጋር በመተባበር እንደሚገነቡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተንግረዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር የአቅርቦት ችግርን ለመፍታም ጥረት ይደረጋል ነዉ ያሉት፡፡

እስካሁን ባለዉ ሂደት የንግድ ስርዓቱ ላይ ችግር እየፈጠሩ ባሉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ የስራ ቦታቸዉ የታሸገባችው፣ የተከሰሱ እና በህግ እየተጠየቁ ያሉ መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡

ለዘላቂ ልማት ግን ‹‹ አንድም መሬት ጦም ማደር የለበትም ›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ ለዚህም ደግሞ ያሉን ቦታዎች ላይ አርሰን ምርትን ማሳደግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *