የብድር አሰጣጥ ሂደቱ ካለፈው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተገለፀ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ እና ማብራሪያ እየሰጡ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት በያዝነው ዓመት እንደ ሀገር 20 በመቶ ማደጉን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ከተሰጠው የብድር መጠን ውስጥ ባለተለመደ መልኩ ከ74 በመቶ በላይ ለግል ሴክተሮች የዋለ መሆን ገልፀዋል፡፡

25 በመቶው የሚሆነው ብድር ደግሞ ለመንግስት ተቋማት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህም ማለት አሁን ለግል ሴክተሮች እየተሰጠ ያለው ትኩረትም ከፍ ማለቱን ያሳያል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒቴር ዶ/ር አብይ ተናግረዋል፡፡

የተሰጡት ብድሮች ቆመው የነበሩ ብዙ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እድንችል አድርጓል ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *