የዘንድሮው ለሓጅና ዑምራህ የሚደረገው ጉዞ በዝቅተኛ ቁጥር የሚደረግ ነው፡፡

የፊታችን ሀምሌ አጋማሽ በሚከበረው የዒድ አል-አድሃ ክብረበዓል ላይ ወደ ሳውዲዋ ቅዱስ ከተማ መካ በመጓዝ የሚከወነው ሃይማኖታዊ ስርዓት (ሓጅና ዑምራህ) ዘንድሮ ገደብ የተቀመጠለት መሆኑን የሀገሪቷ የሓጅና ዑምራህ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ቁጥሩ እንዲቀንስ የሆነውም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።በመላው አለም የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የእስልምና እምነት አማኞች በየአመቱ ወደ መካና መዲና በመጓዝ ሓጅና ዑምራህ በመባል የሚታወቀውን ሃይማኖታዊ ተግባር እንደሚከውኑ ይታወቃል፡፡

በእስልምና እምነት አስተምህሮ፤ አማኞች እንዲያደርጓቸው ግዴታ ከሆኑባቸው ከ5ቱ ትዕዛዛት ውስጥ አንዱ አቅሙ ላላቸው ሰዎች ወደ መካ በመሄድ ሓጅ የሚባለውን ስርዓት መፈፀም እንደሆነ ይገለጻል፡፡

ከአለም ወደ 2.5 ሚሊዮን የሚገመቱ የእምነቱ አማኛች ሃይማኖታዊ ስርዓትን ለመከወን ወደ ሳውዲ የሚያጎርፉ በመሆኑ፤ ለአማኞች ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን የሚወጡበትና በረከት የሚቀበሉበት ከመሆንም ባለፈ ለሳውዲ አረቢያም ቢሆን ትልቅ የገቢ ምንጯም በመሆን ያገለግላል፡፡

የሀገሪቷ የሀጂና ዑምራህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሞሃመድ ባንተን፤ በየትኛውም አለም የሚገኙ አማኞች ዘንድሮ የሚከወነው የሀጅና ዑምራ ስርዓት በዝቀተኛ ቁጥር የሚደረግ መሆኑንና አውቀው የራሳቸውን ጥንቃቄ እንዲደርጉ ማስገንዘብ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ጅብሪል መሐመድ
ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *