ፍላጎት ያላቸው አካላት ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ የበረራ ፍቃድ ተሰጠ::

የኢትዮጵያ መንግስት ፍላጎት ያላቸው አካላት ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ የበረራ ፍቃድ መስጠቱን አስታዉቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ፍላጎት ያላቸው ማንኛውም አካላት ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ ከፈለጉ የበረራ ፍቃድ መስጠቱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡

የበረራ ፈቃዱ ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ እንደተሰጠም ተገልጿል፡፡

ይሁንና አዉሮፕላኖቹ በቀጥታ ወደ ትግራይ ክልል ይግቡ ወይም አዲስ አበባ አርፈዉ ይነሱ የተገለጸ ነገር የለም፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *