በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር “ኢትዮጵያን እናልብስ” የችግኝ መርሃግብር አካሄደ።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በ”ኢትዮጵያ እናልብስ” መርሃ ግብርን በዛሬው እለት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች ፣ሰራተኞችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር ወረዳ በሚገኘው የወፍ ዋሻ ደን ላይ አካሂደዋል።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአረንጓዴ አሻራ የማስጀመሪያ የችግኝ ተከላ በተካሄደበት የወፍ ዋሻ ደን በመገኘት የችግኝ ተከላውን ያስጀመሩት የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶክተር ሒሩት ካሳው ናቸው፡፡

ሚኒስትሯ የዛሬው ችግኝ ተከላ በበጋው ወቅት ቃጠሎ በደረሰባችው ጥብቅ ደኖች ላይ ችግኝ ለመትከል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የያዘው መርሀ ግብር አካል ነው ብለዋል።

በዝቋላ፣በአሰቦትና በየረር ጥብቅ ደኖች ላይ ተመሳሳይ ችግኝ ተከላ ይከናወናል ያሉት ዶክተር ሒሩት ፣ በቃጠሎ የተጎዱ ደኖች ላይ ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ የአካባቢው ማህበረሰብ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን፣ቱሪዝም ኮሚሽንና የብሔራዊ ቴአትር ባለሙያዎችና አመራሮች ተገኝተዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

የውልሰው ገዝሙ

ሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.