የቴሌ ብር ደንበኞች 6.58 ሚሊየን ደረሱ።

በቅርቡ ወደ ስራ የገባው ቴሌ ብር 6.58 ሚሊየን ደንበኞች እንደደረሱ ተነግሯል።

ቴሌ ብር ከተጀመረ ጀምሮ እስካሁን 12.7 ሚሊየን የገንዘብ ልውውጥ እንደነበረም ተገልጿል።

ይህም በሁለት ወር የተመዘገበው ሪፖርት ጥሩ የሚባል ነው ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ።

ኢትዮ ቴሌኮም ለተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች 847 ሚሊየን ብር እንደሰጠ ተገልጿል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የስልክ መልዕክት ለማስተላለፍ እና ማህበረሰቡን ለማገዝ 16 ሚሊየን ብር ወጪ እንደወጣም ተነግሯል።

ገበታ ለሀገር ፕሮግራምም 500 ሚሊየን ብር የሰጠ ሲሆን ለአረንጓዴ ልማትና ለችግኝ ግዢ 20 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ ነው የተገለጸው።

በተጠናቀቀው በጀት አመት ለ337 ሺ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩንም ወ/ሪት ፍሬህይወት ተናግረዋል።

በተጨማሪም በየወሩ 26 ሚሊየን ደንበኞቼን ብድር እየሰጠሁ ነው ሲሉ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

በዚህም 17.4 ቢሊየን ብር ከፍለናል እየተመለሰም በድጋሚም አበድረናል ብለዋል በ2013 በጀት አመት ኢትዮ ቴሌኮም ለሰራተኛና ለተለያዩ ስራዎች 70.8 ቢሊየን ብር ክፍያ እንደፈጸመም ተገልጿል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

መቅደላዊት ደረጄ

ሐምሌ 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *