18 ሚሊዮን አሜሪካውያን ለከፍተኛ የአየር ሙቀት ተገላጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተባለ

በአሜሪካ ምዕራባዊ ክፍሎችና በካናዳ አንዳንድ ግዛቶች ላይ የታየው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ለህይወት አስጊ ከመባል አልፎ ሰዎች ህይወታቸውን እንዲያጡ ሰበብ መሆኑ ከተሰማ ሰነባብቷል፡፡

ይሄው የሙቀት መጠን በተለይም ከአተነፋፈስ ጋር በተያያዘ ተጓዳኝ በሽታዎች ያለባቸው በመቶዎች የሚቀጠሩ የሁለቱንም ሀገራት ሰዎች እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል፡፡

በዚህም በአሜሪካ ምዕራባዊ አቅጣጫ ፤ በኦሬገን፤ በካሊፎኒያና፤ በሞጄቭ በረሃ፤ በኔቫዳና በኡታህ ግዛቶች የሚኖሩ 18 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች የዚሁ ችግር ሰለባ ሊሆኑ እንደቢችሉ ሚካኤል ጋይ የተባሉ የሚትዮሮሎጂ ባለሙያ ለሲኤን ኤን ተናግረዋል፡፡

በአሜሪካ በዲግሪ ፋራናይት እስከ 135 ወይም በዲግሪ ሴንቲግራድ ከ50 በላይ የሚለካ የሙቀት መጠን መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

ይሄው የሙቀት መጠን ደግሞ በተለይ ህመም ላይ የሚገኙ ሰዎችን የመሞት እድላቸውን የሚያፋጥን ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡

የሰዎችን ህይወት ከመቀማቱ ባለፈ፤ ግግር በረዶዎች እየቀለጡ እንደሆነና የባህር ከፍታዎችም እየጨመሩ እንደሆነ እያስተዋልን ነው ብለዋል ሚትዮሮሎጂስቱ፡፡

በተጨማሪም በጫካ ውስጥ የሰደድ እሳት እንዲነሳ በማድረጉ እሳቱ በስድስት ምዕራባዊ ግዛቶች ውስጥ ከ300 ሺህ በላይ ሄክታር በሆነ መሬት ላይ መዛመቱን አስረድተዋል፡፡

ኦሬገን እና ካሊፎርኒያን የሚያገናኘው ከፍተኛ የሀይል መስመር በሰደድ እሳቱ ችግር ውስጥ ሊገባ እንደሚችልም አመላክተዋል ባለሙያው፡፡

ላለፉት ሶስት ቀናት በእያንዳንዱ ቀን እሳቱ በእጥፍ ማደጉ የተገለጸ ሲሆን በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ቦታውን ለመልቀቅ እንዲዘጋጁ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ጂብሪል መሀመድ

ሐምሌ 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *