“ግብር ከፋዮች ትክክለኛ ስልክ አለማስመዝገባቸው ችግር ሆኖብኛል” – የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮየአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የ2013 ዓ.ም “የደረጃ ሐ” የገቢ ግብር ከፋዮችን ለማስተናገድ አጭር የጽሁፍ መልዕክት እንዲደርሳቸው በማድረግ ና ግብራቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል እንዲከፍሉ የጀመርኩት አሰራር ፤ግብር ከፋዮች ትክክለኛ ስልክ አለማስመዝገባቸው እንቅፋት እንደሆነበት ገልጿል፡፡

ከአጭር የጽሁፍ መልዕክት ውጪ የኔትዎርክ መቆራረጥም ተጨማሪ እንቅፋት እንደሆነ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ረታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ግብር ከፋዮች በ7075 አጭር የጽሁፍ መልዕክት ሲደርሳቸው የተላከላቸውን የግብር መጠን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመክፈል ክሊራንስ እንዲወስዱ የተጀመረ አሰራር እንዳለ ተናግረው፣ ወረዳዎች የሚገኙበት ቦታ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት አለመኖር ለአሰራሩ ችግር እንደፈጠረባቸውም አብራርተዋል አቶ ተስፋዬ።

ይህን ችግር ለመቅረፍም ከኢትዮ ቴሌኮም ከመብራት ሀይልና ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር እየሰራን ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ ሶስት መቶ ሺ የሚደርሱ የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች መኖራቸው የተገለጸ ሲሆን ለ164ሺህ የግብር ከፋዮች ውሳኔ መሰጠቱም ተገልጿል።

ከነዚህም ውስጥ ለ106 ሺ 695 ግብር ከፋዮች የአጭር የጽሁፍ መልዕክት እንደደረሳቸው ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *