አሜሪካ በአፍጋኒስታን በነበራት ተልዕኮ በአስተርጓሚነት ሲገለግሏት የነበሩትን የአፍጋን ዜጎች ይዛቸው እንደምትወጣ አስታወቀች፡፡

ይህ እርምጃ ደኅንነታቸው ለመጠበቅ የሚወሰድ ስለመሆኑ የጆ ባደን አስተዳደር አሳውቋል፡፡

ለ20 አመታት በአፍጋኒስታን የቆየው የአሜሪካ ጦር በፕሬዝደንት ጆ ባይደን ትዕዛዝ ከመስከረም 11 በፊት ሙሉ በሙሉ ተጠቃሎ እንዲወጣ ተወስኗል፡፡

የአሜሪካ ወታደሮች መውጣታቸውን ተከትሎም እስላማዊ ታጣቂ ቡድኑ ታሊባን ባለፉት ሳምንታት በርካታ የአፍጋኒስታን አካባቢዎችን መቆጣጠሩ ተነግሯል እንደ ቢቢሲ ዘገባ፡፡

የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ “እንግሊዝኛ አስተርጓሚ የነበሩ አፍጋኒስታዊያን ለእኛ ጀግኖች ናቸው፡፡ ”ለዚህ ታላቅ ስራቸው እውቅናና ዋጋ መስጠት እንፈልጋለን” ብለዋል ፡፡

አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለሮይተርስ ተናገሩ እንደተባለው 2ሺ 500 የመሆኑና በአስተርጓሚነት ያገለገሉ አፍጋኒስታናዊያን ለጊዜው በአሜሪካ ወታደራዊ ካምፖች ወይም በሌላ ሦስተኛ አገር እንዲቆዩ ተደርጎ የቪዛ ሒደቱ እየተፈጸመላቸው ነው፡፡

የሚያገኙት የቪዛ አይነትም ‹ልዩ የኢሚግራንት ቪዛ› ይሆናል ተብሏል፡፡የአሜሪካን ሰራዊት ከአፍጋኒስታን መውጣት ተከትሎ በነዚህ አስተርጓሚዎች ላይ ታሊባን የበቀል እርምጃ ሊወስድ ይችላል የሚል ፍራቻ አለ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ያይኔአበባ ሻምበል

ሐምሌ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *