ሕብረት ባንክ የ ISO/IEC 27001፡ 2013 ሰርተፊኬት ተሸላሚ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የባንኩ የአይሲቲ መሰረተ ልማት ክፍል ዳይሬክተር አቶ ዑስማን ሰኢድ እንዳሉት፣ባንኩ በኦንላይን ባንኪንግ፣በዳታ ሴንተርና በዲዛስተር ሪከቨሪ ፋሲልቲ የመረጃ ደህንነት አስተዳደር የ ISO/IEC 270001:2013 መስፈርትን በማሟላቱና አስተማማኝ የደህንነት ስርዓት በመዘርጋቱ ሽልማቱ እንደተሰጠዉ ተነግሯል፡፡

ይህም ባንኩን በኢትዮጵያ ከሚገኙ ባንኮች ይህን እዉቅና በማግኘት ቀዳሚዉ ያደርገዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አቶ ዑስማን እንዳሉት ባንኩ ያገኘዉ ሰርተፊኬት በሚሰጣቸዉ የኦንላይን ባንኪንግ አገልግሎቶች አስተማማኝ ስርዓት መዘርጋቱን የሚያረጋግጥና ደንበኞች አስተማማኝ የሆነ የኦንላይን ባንኪንግ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ማሳያ ነዉ ብለዋል፡፡

ከዚህ ባሻገርም የፋይናንስና ሌሎች የባንኩ መረጃዎች ደህንነታቸዉ የተጠበቀ መሆኑን የሚያረጋግጥ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የአስተዳደር ስርዓቶችን በዓለም አቀፍ መመዘኛዎች በመገምገም የማረጋገጫ ሰርተፊኬት በመስጠት የሚታወቀዉ “Professional Evaluation and Certification Board” ወይም በምህጻሩ “PECB MS” ድርጅት ባንኩን በተቀመጡ የ ISO/IEC 27001፡2013 መስፈርቶች መሰረት የባንኩን የመረጃ ደህንነት ስርዓት በመመርመር ባንኩ ሰርቲፋይድ መሆኑን ማረጋገጫ መስጠቱም ተጠቁሟል፡፡

ባንኩ ያገኘዉ ሰርተፊኬት ለቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት የሚያገለግል መሆኑንም ሰምተናል፡፡

ይህም በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን እያደገ ከመጣዉ የሳይበር ጥቃት አንጻር፣ባንኩ ለደንበኞቹ የተቀላጠፈና አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጥ ያስችለዋል ተብሏል፡፡

ISO/IEC 27001፣በድርጅታዊ የመረጃ ደህንነት አስተዳደር ስርዓት ዉስጥ ህጋዊ፣ አካላዊ፣ አስተዳደራዊ እና ቴክኒካዊ ጉዳዮችን እንዲሁም የሰዉ ሃይልና የፋይናንስ አያያዝ ስርዓትን በመፈተሽ የሚሰጥ የደህንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ሐምሌ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *