የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በኮቪድ19 እና በፀጥታ ችግር ምክንያት ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ያገኝ ነበረዉን ገቢ አለማግኘቱ ተነግሯል፡፡
የፓርኩ ኃላፊ አቶ አበባዉ ኣዛናዉ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ የኮቪድ ወረርሽኝ ከ 9 ሺህ በላይ በሚሆኑ የአካባቢዉ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልፀዋል፡፡
ኮቪድ ከመከሰቱ በፊት ፓርኩ የአካባቢዉ ነዋሪዎች በተለያዩ አገልግሎቶች ከ50 እስከ 60 ሚሊዮን ብበር በአመት ያገኙ እንደነበር ያስታወሱት አቶ አበባዉ ከዚህ በተጨማሪም ፓርኩ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ ሲያደርግ መቆየቱን ለኢትዩ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጅ ባለፈዉ አመት የኮቪድ 19 መከሰቱን ተከትሎ የጎብኚዎች ፍሰት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ቆሟል ነዉ የተባለዉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በነበረዉ የህግ ማስከበር ዘመቻ በተፈጠረዉ የፖለቲካ አመረጋጋት ምክንያት ጎብኚዎቹ ወደ ፓርኩ እንዳይመጡ ማድረጉም ተነስቷል፡፡
ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህም በተለያዩ አገልግሎቶች ከፓርኩ ይጠቀሙ የነበሩ ከ9 ሺህ በላይ የአካባቢዉ ነዋሪዎችም የችግሩ ተጠቂ መሆናቸዉን ኃላፊዉ ያክላሉ፡፡
ከዚህ ባለፈ ግን በ2011 ዓ.ም ፓርኩ ተከስቶ በነበረዉ የእሳት አደጋ ፓርኩ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ሙሉ በሙሉ ማገገሙን አቶ አበባዉ ተናግረዋል፡፡
ፓርኩ ከእሳት አደጋዉ ሊያገግም የቻለዉ የተለያዩ ችግኞችን በመትከልና የጥበቃ ስራዉ ተጠናክሮ በመቀጠሉ እንደሆነም ሰምተናል፡፡
በቀጣዩ ሳምንትም በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከ25 ሺህ በላይ ችግኞችን የመትከል ስራ እንደሚከናወንም ታዉቋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
አባቱ መረቀ
ሐምሌ 08 ቀን 2013 ዓ.ም
