የጀርመኗ መርሃይተ መንግስት በአፍጋኒስታን ጣልቃ ገብተን ከ20 አመታት በላይ ብንቆይም አገር ግን መገንባት አልቻልንም አሉ

የጀርመኗ መርሃይተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በአሜሪካ መሪነት አፍጋኒስታንን ለመገንባት ከ20 አመታት በላይ ብንቆይም ያንን ማድረግ ግን ሳንችል ወጥተናል ብለዋል፡፡

ሜርክል ይህንን ያሉት ከአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በነጩ ቤተመንግስት በሰጡት መግለጫ ነዉ፡፡
ባለፉት 20 አመት ቆይታችን ሽብርተኞች ሊያደርሱ የሚችሉ ጥፋቶችን ቀንሰን ይሆናል ፣ነገር ግን የምንፈልገዉን ነገር አሳክተናል ማለት ግን አንችልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአፍጋኒስታን ምድር 160 ሺህ በላይ የጀርመን ወታደሮች መቆየታቸዉ የተነገረ ሲሆን በዚህም 59 ወታደሮች መሰዋታቸውን ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ጀርመን ለአፍጋኒስታኑ ወታደራዊ ተልዕኮ 14.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ስለማዉጣቷም የዘገበዉ አናዶሉ ኤጀንሲ ነዉ፡፡

አሜሪካ መራሹ ጦር ከ95 በመቶ በላይ የአፍጋንን ምድር ለቆ መዉጣቱ የተነገረ ሲሆን እስከ ቀጣዩ ነሃሴ መጨረሻ ድረስ ጦሩ ሙሉ በሙሉ እንደሚወጣ ተገልጿል፡፡

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እኛ አፍናጊስታን የዘመትነዉ አገር ልንገነባ አልነበረም ማለታቸዉም መነጋጋሪያ መሆኑ የሚታወስ ነዉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

አባቱ መረቀ
ሐምሌ 09 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *