ሞሮኮ የፈረንሳዩን ፕሬዝዳንት ማክሮንን ስልክ ለመጥለፍ ሙከራ አደረገች

ከፈረንሳይ የሚወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሞሮኮ ሰላዮች ስልካቸው የጠለፋ ሙከራ ተደርጎበት ነበር፡፡

ስልክ ላይ በሚጫነው እስራኤል ሰራሹ ፔጋሰስ የተባለ የሳይበር ጥቃት ማድረሻ ሶፍትዌር ነው ሞሮኮ የማክሮንን ስልክ ልትጠልፍ የሞከረችው፡፡

የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኤዶውአርድ ፊልፔን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ሚኒስትሮች የዚሁ ጥቃት ሙከራ እንደደረሰባቸው ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

የነዚህ ባለስልጣናት ቁጥር ሶፍትዌሩ አስሶ እንዲያጠቃቸው ከተዘረዘሩ 50 ሺህ የሚሆኑ ስልኮች መካከል ነው፡፡

የዚህ የስለላ ሶፍትዌር መስራቾች፤ መንግስት ሽብርተኝነትንና ወንጀልን እንዲታገልበት ብቻ ነበር መሳርያውን የሸጥነው እያሉ ነው እንደ ቢቢሲ ዘገባ፡፡

የፈረንሳዩ ጋዜጣ ሌሞንዴ፤ ማክሮን ስልኩን እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2017 ጀምሮ ይጠቀሙበት ነበር ሲል ዘግቧል፡፡

ከፈረንሳይ እንደወጣው ሪፖርት ከሆነ፤ በዚህ ጥቃት ወይም ሀክ ሙከራ ከተደረገባቸው መካከል የደቡብ አፍሪካው ሲሪል ራማፎዛ፣የኢራቁ ፕሬዝዳንት ባራም ሳሊህ፣የግብፅ፣ የፓኪስታን እና የሞሮኮ ጠቅላይ ሚኒስትሮች እና የሞሮኮ ንጉስ ይገኙበታል፡፡

ባጠቃላይ ከ 34 ሀገራት የሚሆኑ 600 የመንግስት ባለስልጣናትና ፖለቲከኞች የሀኪንጉ/የጠለፋው ሙከራ ተደርጎባቸዋል ተብሏል፡፡

ሪፖርቱ ተመርምሮ እውነት ሆኖ ከተገኘ ምላሹ ጠንከር ያለ እንደሚሆን አመላክተዋል የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ አስራት
ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.