የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የደረጃ ስያሜ መመሪያ ማክበርን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ መሰረት፣ ካሉት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ዩኒቨርሲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ኮሌጅ እና ኢንስቲትዩት የሚል የደረጃ ስያሜ ካላቸው ውጪ ፤ዩኒቨርሲቲና ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እያሉ መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ገልጧል፡፡
በዚህም መሰረት
ዩኒቨርሲቲ የሚል የደረጃ ስያሜ ያላቸው እስካሁን 5 ሲሆኑ እነርሱም፡-
- ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ
- ቅድስተ-ማርያም ዩኒቨርሲቲ
- ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ
- ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ እና
- አድማስ ዩኒቨርሲቲ ናቸው፡፡
ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ስያሜ ያላቸው የግል ተቋማት እስካሁን 5 ሲሆኑ እነዚህም ፦
- አልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ
- ኒው ጀነሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ
- ሸባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ
- ሆፕ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ
- ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ናቸው፡፡
የተቀሩት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮሌጅ ወይም ኢንስቲትዩት የሚል የደረጃ ስያሜ ያላቸው ናቸው ብሏል፡፡
ከላይ ከተጠቀሰው ውጪ ከደረጃ ስያሜ ውጪ ባልተፈቀደ የደረጃ ስያሜ በመገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያ ማሰራት፣ በተለያዩ ሰነዶች እና ባነሮች ላይ መጠቀም፤ ማዕተም ማሰራት ወዘተ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ኤጀንሲው አሳውቋል።
ባልተፈቀደ የደረጃ ስያሜ የተሰጠ የትምህርት ማስረጃ ካለም ተቀባይነት አይኖረውም ተብሏል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 20 ቀን 2013 ዓ.ም
