“ወጣቶች ከጎሳና ብሄር አስተሳሰብ ወጥተው ለኢትዮጵያውነት መቆም አለባቸው” አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን

ወጣቶች ከጎሳና ብሄር አስተሳሰብ ወጥተው ለኢትዮጵያውነት መቆም አለባቸው ሲል የክብር ዶክትሬት ሽልማቱን ከጎንደር ዩንቨርስቲ በዛሬው እለት የተሸለመው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

የክብር ዶክትሬት ሽልማቱ የዪንቨርሲቲ ሴኔት በወሰነው መሰረት የሂዩማን ሊትሬቸር የክብር ዶክትሬት ሽልማቱን በ6 ሺህ 5መቶ 74 ተማሪዎችን ፊት ተቀብሏል።

አርቲስት ቴዲ አፍሮ በመድረኩ ላይ ባደረገው ንግግር ዪንቨርሲቲውን አመስግኖ ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ ያላቸሁ መልዕክቱን ያስተላለፈ ሲሆን ወጣቶች ከጎሳና ብሄር አስተሳሰብ ወጥተው ለኢትዮጵያውነት እንዲቆሙ ጠይቋል ።

ከክብር ዶክትሬት ሽልማቱ በተጨማሪም አርቲስት ቴዲ አፍሮና ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ ከጎንደር ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን የክብር ካባ ተበርክቶላቸዋል ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

አባቱ መረቀ
ሐምሌ 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *