በአማራ ክልል የተፈናቃዩች ቁጥር 1.2 ሚሊዮን ደረሰ 

ህውሓት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ወረራ በማድረጉ ምክንያት ግጭቱን ፈርተው 200ሺህ ዜጎች በራያ ፤በወልቃይት እና አካባቢው እንዲሁም ከሌሎች ሶስት ግንባሮች መፈናቀላቸውን እና ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ሶስት አመታት ህውሓት ሲሰራው በነበረው ሴራ በተነሱት ግጭቶች ምክንያት ከተፈናቀሉ ሰዎች ጋር ሲደመር በክልሉ ያለው የተፈናቃይ ቁጥር 1.2 ሚሊየን እንደደረሰ አቶ ግዛቸው ገልጸዋል፡፡

ይህ ደግሞ በየወሩ 150 ሺህ ኩንታል እህል የክልሉ መንግስት እንዲያቀርብ አስገድዶታል ብለውናል፡፡

ከለጋሽ አለም አቀፍ ተቋማት አንድም ቀን የሰብአዊ እርዳታ እንዳላገኙ የሚናገሩት ሃላፊው በክልሉ ባሉ የሀይማኖት ተቋማት እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በውጪ ያሉ ሀገር ወዳድ ዜጎች ድጋፍ እያገኙ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ተፈናቃዮች በመጠለያ ካፕ ማስቀመጥ ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዙ ከባድ በመሆኑ የአማራ ክልል መንግስት ብቻውን የሚወጣው ባለመሆኑ፣የክልሉ ነዋሪዎች በአቅማቸው እኚህን ወገኖች ሰብስቦ በመያዝ የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

በክልሉ ያለው የተፈናቃዮች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም አንድም ቀን የምዕራቡ አለም መገናኛ ብዙሀን ሽፋን ሰጥተውት እንደማያውቁ የሚናገሩት አቶ ግዛቸው ይህ ደግሞ ሆን ተብሉ የተፈጸመ ሌላኛው ሴራ ነው ብለውታል፡፡

ተፈናቃዮች የጤና የምግብ እና የመጠለያ ችግሮች እዳይገጥማቸው ግን የክልሉ መንግስት እና የአማራ ክልል ነዋሪ ትልቅ ስራ እየሰራ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ያይኔ አበባ ሻምበል
ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *