ሳማንታ ፖዎር ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ከጠቅላይ ሚኒስትር ጋር እንደማይገናኙ ተነግሯቸዉ ነበር— የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ኃላፊ ሳማንታ ፖዎር ከጠቅላይ ሚንስትሩ እና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ለመወያየት ጥያቄ ቢያቀርቡም መሪዎቹ በስራ መደራረብ ምክንያት ማግኘት እንደማይችሉ ቀድሞው ተነግሯቸዉ ነበር ተብሏል ።

ኃላፊዋ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡም ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር እንደማይገናኙ ተረድተው ነው የመጡት ብለዋል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ።

ሳማንታ ፖዎር የፖለተካ ኃላፊ ሳይሆኑ የተራድኦ ድርጅት ኃላፊ በመሆናቸው ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሃላፊዎች ጋር ጥሩ ውይይት ስለመደረጉም ተነስቷል።

በቆይታቸው ከሠላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደው ወደ አገራቸው መመለሳቸውንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

ሳማንታ ፖዎር በሱዳን በኩል ያለው ድንበር ይከፈት የሚል ሃሳብ በውይይቱ ወቅት እንዳላነሱም ታውቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *